ከደረጃ በታች የሆኑ ምርቶች እንዳይገቡ መታገድ

ነሐሴ 29/2013 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ በቅርቡ በአስገዳጅነት ደረጃ እንዲወጣላቸው ከተደረጉ ምርቶች መካከል ዲቫይደርና ሃይል ቆጣቢ አምፖሎች የኢትዮጵያን ደረጃ ባለማሟላታቸው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታገዱ፡፡

ምርቶቹ በአስገዳጅነት ደረጃ ከወጣላቸው በኋላ አምራቾቹ በወጣላቸው ደረጃ መሰረት ማስተካከያ እንዲያደርጉ ለ4 ወራት የእፎይታ ጊዜ ተሰጥቷቸው ነበር፡፡

በዚህም መሰረት ኤጀንሲው ከሐምሌ 1/2013 ጀምሮ ወደ ቁጥጥር የገባ ሲሆን፥ ቁጥጥር በሚደረግበት ጊዜ የተጠቀሱት ምርቶች በቤተ ሙከራ ፍተሻ በሚደረግበት ጊዜ የኢትዮጵያን ደረጃ ሳያሟሉ ቀርተዋል ነው የተባለው፡፡

በፍተሻ ወቅት 21 የኃይል ማከፋፈያ (ዲቫይደር) አይነቶች ከፍተኛ ኃይል የሚጠቀሙ፣ ኃይል የሌላቸውና የተላላጡ ሆነው መገኘታቸውን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።