ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች የተካተቱበት የልዑካን ቡድን ድሬዳዋ ገብቷል


ግንቦት 12/2014 (ዋልታ)
ፕሬስ ድርጅት ባዘጋጀው ሁለተኛው ዙር “ስለኢትዮጵያ” የፓናል ውይይትና የፎቶ ግራፍ አውደርዕይ ላይ ለመታደም ከፍተኛ የፌዴራል መንግሥት አመራሮችን የያዘ የልዑካን ቡድን ድሬዳዋ ከተማ ገብቷል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነሩ ደበሌ ቃበታ ድሬዳዋ ከገባው ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ቡድን መካከል ይገኙበታል።
ተሳታፊዎቹ ድሬዳዋ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር ፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጌትነት ታደሰና ሌሎች የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
“ስለኢትዮጵያ” የተሰኘው የፎቶግራፍ አውደ ርዕይና የፓናል ውይይት በነገው ዕለት በከተማዋ እንደሚከፈት ኢፕድ ዘግቧል።