ከፑሽኪን አደባባይ – ጎተራ ማሳለጫ መንገድ 2ኛ ደረጃ የአስፋልት ንጣፍ ስራ እየተከናወነ ነው

ፑሽኪን አደባባይ – ጎተራ ማሳለጫ መንገድ

ኅዳር 6/2014 (ዋልታ) የፑሽኪን አደባባይ – ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት ሁለተኛ ደረጃ የአስፋልት ንጣፍ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በቻይና ፈርስት ሀይ ዌይ ኢንጂነሪንግ በተባለ የስራ ተቋራጭ እያስገነባው ያለው የመንገድ ፕሮጀክቱ የመጨረሻው የአስፋልት ንጣፍ ስራ ነው እየተከናወነለት ይገኛል ነው የተባለው።

የመንገድ ፕሮጀክቱ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ ሲሆን ግንባታው መስከረም 20 ቀን 2012 ዓ.ም መጀመሩን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።