ክፍለ ከተማው ከ10ሺህ በላይ ለሚሆኑ የእስልምና እምነት ተከታዮች ማዕድ አጋራ

ሚያዚያ 22/2014 (ዋልታ) የአቃቂ ቃሊቲ ክፍል ከተማ የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ10 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ የእስልምና እምነት ተከታዮች ማዕድ የማጋራት መርኃግብር አካሄደ።

ክፍለ ከተማው ከዚህ ቀደምም የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ማዕድ ማጋራቱ ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ዣንጥራር አባይ የከተማ አስተዳድሩ የኑሮ ውድነትን ለማቃለል እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ነድፎ እየሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ከዚያ ጎን ለጎንም የአብሮነት እና ወንድማማችነትን ሰሜት ለማጠናከር የመደጋገፍ እሴቶች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍል ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሀቢባ ሲራጅ በበኩላቸው በክፍለከተማው ከ36 ሺህ በላይ ድጋፍ የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡

የትንሳኤ እና የኢድ አልፈጥር በአላትን ምክንያት በማድረግ በክፍለ ከተማው ያሉ ባለሀብቶችን በማስተባበር ከ29 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወገኖች ማእድ ማጋራት ተችሏል ብለዋል።

በመስከረም ቸርነት