ኮሚሽኑ ዲጅታል የመረጃ እና እውቀት ማዕከል ፖርታል የአሰራር ስርዓትን ይፋ አደረገ

ሚያዚያ 28/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ዲጅታል የመረጃ እና እውቀት ማዕከል ፖርታል የአሰራር ስርዓትን ይፋ አደርጓል።

የመረጃ እውነተኛነትን ያጎለብታል የተባለለት የመረጃ ቋቱ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን እየሰራ ያለውን ብሎም በመላ ሀገሪቱ የሚገኘውን ትክክለኛ መረጃ በቀላሉ ማግኘት እንደሚያስችል ተገልጷል ።

ከዚህ ቀደም በመረጃ አሰጣጥ ስርዓት ውስጥ በነበረ ክፍተት የመረጃ ቋቱ ለሀሰተኛ መረጃ የተጋለጠ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን፤ ይፋ የተደረገው ዲጅታል ላይብረሪ ይሄንን ያስቀራል ተብሎ ይታመናል።

የዌብ ፖርታል እና የዲጅታል ላይብረሪው ስራ በስድስት ዓመት የተጠናቀቀ ሲሆን በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት የሰብዓዊ ድጋፍ ስለሚሹ አካላት መረጃን በቀላሉ ማግኘት የሚያስችል እንደሆነ ተጠቅሷል።

አዲሱ የመረጃ ቋት ክልልሎችና ወረዳዎችን በመረጃ የሚያስተሳስር ሲሆን የተፈጥሮ አደጋ ከመከሰቱ በፊት ቅድመ ጥንቃቄን ለመውሰድ ብሎም ህብረተሰቡን ከከፋ አደጋ ለመታደግ ያስችላልም ተብላል።

 

በሃኒ አበበ