ኮርፖሬሽኑ በሀገሪቱ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉ ምቹ ሁኔታዎችን ለባለሀብቶች አስጎበኘ

ጥቅምት 3/2015 (ዋልታ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሀገሪቱ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉ ምቹ ሁኔታዎችን ለባለሀብቶች አስጎበኘ።

የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት ለማድረግ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን የጎበኙ ሲሆን በዋናነት በፋርማሲቲካል ዘርፍ ያሉ ባለሀብቶች በፓርኩ ኢንቨስት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ቂሊንጦ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በርካታ መሰረተ ልማቶች የተሟሉለት በመሆኑ ባላሃብቶች ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በብርቱካን መልካሙ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW