ኮርፖሬሽኑ በቀበና ያስገነባውን የመኖሪያ መንደር አስመረቀ

ሰኔ 5/2014 (ዋልታ) የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በቀበና ያስገነባውን ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር የቀበና ሳይት ፕሮጀክት አስመረቀ፡፡

ሳይቱ በተቀመጠለት የውል ጊዜ፣ ወጪና ጥራት መሠረት የተገነባ ዘመናዊ ሕንጻ ሲሆን አጠቃላይ 1ሺሕ 727 ካሬ ሜትር ይዞታ ያለው 1ሺሕ 167 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ባለ 2 ብሎክ G+10 ሕንፃ ነው፡፡

ቤቶቹ ስፋታቸው ከ70 ካሬ ሜትር እስከ 185 ካሬ ሜትር የሚደርሱ ሲሆን ከባለ 1 እስከ ባለ 4 መኝታ ክፍል ያላቸው ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ናቸው፡፡

የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አይሻ መሀመድ፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)፣ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ረሻድ ከማል እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከቀበና ሳይት በተጨማሪ በገርጂ ያስገነባውን ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር ፕሮጀክት በደማቅ ሁኔታ በይፋ የሚያስመርቅ ይሆናል፡፡

በሰለሞን በየነ