ወልድያን ለመቆጣጠር የመጣዉ የአሸባሪው ታጣቂ ኃይል እየተደመሰሰ መሆኑ ተገለጸ

ነሃሴ 06/2013 (ዋልታ) –  ወልድያን ለመቆጣጠር አሠፍስፎ የመጣው የአሸባሪውን የህወሓት ታጣቂ ኃይል በጉባ ላፍቶ ወረዳና አካባቢው በከፍተኛ የጀግንነት ስሜት በመደምሠሥ ላይ እንደሚገኝ ጀግናው የደቡብ ዕዝ የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር አሰታወቀ።

የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ እንደገለፁት ፣ አሸባሪው የጁንታ ቡድንና ርዝራዦቹ ትላንት በመከላከያ ሠራዊት የደረሠበትን አይቀጡ ቅጣት በመዘንጋት በሽብር ተግባር ዳግም የቅዠት ህልሙን አሣካለሁ ብሎ ዓለም አቀፍ ህግን በመጣሥ ህፃናትን ወደ ጦርነት እያሠለፈና እየማገደ እንቅሥቃሤ ለማድረግ ቢሞክርም በጀግናው የ21ኛ ጉና ክ/ጦር የሠራዊት አባላት ሣንቃ በተባለው እና በጉባ ላፍቶ ወረዳአ ካባቢ የሽብር ቡድን አባላትን ድባቅ በመምታት መደምሠስ ተችሏል።

በህዝባችን ጠንካራ የደጀን ደጋፍ አና በጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ብርቱ ክንድ ኢትዮጵያን ለመበተን አፈር ልሼ እነሣለሁ ብሎ የሚፍጨረጨረውን ጁንታ ግብዓተ መሬቱን ለመፈፀም ሠራዊታችንና ህዝባችን ከጫፍ እሥከ ጫፍ ቀን ከሌት ሣይሉ አሸባሪውን የሽንፈት ፅዋ እያሥጎነጩት ነው ያሉት::

ዋና አዛዡ ትላንትም ዛሬም ለጠላቱ ግንባሩን የማያጥፈው ጀግናው የ21ኛ ክ/ጦር ሠራዊት በሰሞነኛው የሥኬትና የጀግንነት ውሎ በጭፍን ተነሣስቶና በከንቱ ህልም ተገፋፍቶ የሚገጥመውን እሣት በሚገባ ሣይረዳ የመጣውን አሸባሪ ሀይልና ባንዳ በመደምሠስ ታላቅ የጀግንነት ተግባር ፈፅሟል ሢሉ ገልፀዋል፡፡

አሸባሪው በሣንቃ በጉባ ላፍቶና እና በአራዶም ተራራና አካባቢው ጥቃት ለማድረስ አስቦ የነበረ ቢሆንም ጀግናው የ21ኛ ክፍለ ጦር ዓባላት በርካቶችን በመደምሠስ ቀላል የማይባል የጦር መሣሪያ መማረክ መቻላቸውን አዛዡ ጨምረው ገልፀዋል።

አዛዡ አክለውም ፣ ጁንታው ወልድያን ተቆጣጥሪያለሁ ያለውን ሀሠተኛ ወሬ በማሥታወስ በአሁኑ ሠዓት ወልድያ ላይ ሁነን እንኳን የሀሠት ወሬውን በመንዛት ይህን ቦታ ይዣለሁ ይህንን አካባቢ ተቆጣጥሪያለሁ እያለ ህዝብን የሚያሸብር ተግባሩን እንደ አንድ የጦርነት ሥልት እየተጠቀመበት ነው ብለዋል::

ስለሆነም ህዝባችን በአሸባሪው “የበሬ ወለደ”ወሬ ሣይደናገርና ሣይረበሽ ከሠራዊቱ ጎን በመሆን ተቀጣጥሎ የቀጠለውን ህዝባዊ ድጋፉን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

ከአሁን ቀደም ጁንታው ከአንዴም ሁለት ሦስቴ 21ኛ ጉና ክፍለ ጦርን ሙሉ በሙሉ ደሥሻለሁ ብሎ እነደነበር አስታውሰዋል።

የ21ኛ ክፍለ ጦር የሠራዊት አባላት አሁንም በአሥተማማኝ የዝግጁነት ቁመና ላይ እንደሆነ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።