ወሎ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው

መጋቢት 12/2014 (ዋልታ) በአሸባሪው ሕወሓት የጥፋት ቡድን ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት መልሶ ለማስቀጠል ወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።
ዩኒቨርሲቲው ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ነባር ተማሪዎችን እየተቀበለ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ተማሪዎች ስለዩኒቨርሲቲው ይሰሙት የነበረውን የውድመት መጠን መልሶ በመገንባት ያለበት ሁኔታ እንዳስገረማቸው ተናግረዋል።
የተማሪ ወላጆች በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ወደ ቀድሞ ገጽታው በመመለሱ ያለስጋት ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲልኩ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ አመላክቷል::