ዋልታ ከአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በጋራ ለመሥራት ተስማማ

የካቲት 10/2014 (ዋልታ) ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት እና የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

የባለስልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ደሳለኝ ፉፋ ከዚህ ቀደም ስለተቋሙ በሰዎች ዘንድ የተዛባ አመለካከት እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም ከዋልታ ጋር በመሆን ችግሮች ላይ ጥናት በማድረግ ያለውን የተዛባ አመለካከት መቀየር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ንጉሴ መሸሻ (ዶ/ር) በበኩላቸው ዋልታ በጥናት የካበተ ልምድ እንዳለው አንስተው የሚስተዋሉ ችግሮችን በጥናት በመለየት ግንዛቤ ለመፍጠር በጋራ መሥራት እንደሚቻል ገልጸዋል።

ባለስልጣኑ በ2005 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችና ህግ ያስከብራል እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ይሰራል።

በመስከረም ቸርነት