ውጫሌና ኡርጌሳ ከተሞች ተቋርጦባቸው የቆየውን ኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም አገኙ

ጥር 12/2014 (ዋልታ) ውጫሌና ኡርጌሳ ከተሞች በሽብር ቡድኑ ሕወሓት ተቋርጦባቸው የቆየውን የኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ ዳግም ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

ከተሞቹ ተቋርጦባቸው የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል እንደገና ማግኘት መቻላቸውን የወልዲያ ዲስትሪክት ዳይሬክተር ሽመልስ ወ/ሰማያት ተናግረዋል።

ቡድኑ 84 ኪሎ ሜትር በሚረዝመው የደሴ-ወልዲያ 66 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመር ላይ ጉዳት ማድረሱን ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡