ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በትግራይ ድጋፍ አደረገ

መጋቢት 01/2013 (ዋልታ) – ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ለተፈናቀሉ 9 ሺህ 125 አባወራዎች ድጋፍ አደረገ፡፡

ከዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ድረ ገጽ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ኮሚቴው በሰሜን ትግራይ በአዲግራት፣ አድዋ፣ አክሱም እና ሽረ ለሚገኙ ስምንት ሆስፒታሎች የህክምና ቁሳቁሶችን አከፋፍሏል፡፡