ዓለም ዐቀፍ የቀይ መስቀል እና የቀይ ጨረቃ ቀን በኢትዮጵያ ተከበር

ሚያዝያ 29/2014 (ዋልታ) የዓለም ቀይ መስቀል እና የቀይ ጨረቃ ቀን በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ለ75ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ64ኛ ጊዜ “ደግነት ለሰብዓዊነት” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር “ደግነት ለሰብአዊነት” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ እስታድየም አከባቢ የጽዳት መርኃ ግብር በማከናወን ቀኑን አክብሯል።

የማኅበሩ ዋና ጸሃፊ ጌታቸው ተኣ፤ ማኅበሩ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ሁሉም ማኅበሩን ሊደግፍ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በጽዳት መርኃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች ፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የብሔራዊና የአዲስ አበባ ቅርንጫፎች አመራር ቦርድ አባላት ተገኝተዋል።

በእመቤት ንጉሴ