ዕጩ መኮንኖች የአሸናፊነት ሥነ-ልቦና መላበስ ይገባቸዋል – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ግንቦት 21/2014 (ዋልታ) ተመራቂ ዕጩ መኮንኖች የአሸናፊነት ሥነ-ልቦና መላበስ እንደሚገባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ያሰለጠናቸው ዕጩ መኮንኖች ምረቃ ላይ በመገኘት ንግግር አድርገዋል፡፡

በንግግራቸውም የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ለመሆንና ሀገርን ለማገልገል የወሰናችሁ በመሆኑ ልትመሰገኑ ይገባል ብለዋል፡፡

በመሆኑም እጩ ተመራቂዎች ጀግንነትን፣ ዓላማ እና የማይነጥፍ ዕውቀትን ማንገብ እንደሚገባቸው ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁል ጊዜም ቢሆን የአሸናፊነት ሥነ-ልቦና መላበስ የሚገባ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

ቀድሞም ቢሆን ኢትዮጵያ ሁል ጊዜ የሚገጥሟትን ጠላቶች ስታሸንፍ ኖራለች ያሉ ሲሆን ዛሬም ነገም አሸናፊ እንደሆንን እንቀጥላን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ያሰለጠናቸው ዕጩ መኮንኖችም ሀገር የጣለችባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ እንዲሆኑ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

በሰለሞን በየነ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW