ዛሬ 1ሺሕ 355 ዜጎች ከሳኡዲ አረቢያ ተመለሱ

ሚያዝያ 3/2014 (ዋልታ) በዛሬው ዕለት 1ሺሕ 355 ዜጎች ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ተገለጸ፡፡

በዚህም ከተመለሱት 350 ህጻናት ሲሆኑ 1 ሺሕ 5 ሴቶች መሆናቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ለተመላሾቹ አስፈላጊውን ድጋፍና እንክብካቤ ከተደረገላቸው በኋላ ወደ ጊዚያዊ ማቆያ ማእከል እንዲሄዱ መደረጉንም የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!