ዜጎች በዲጂታል መታወቂያ ላይ እንዲተማመኑ የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎች እየተዘጋጁ መሆናቸው ተጠቆመ

መጋቢት 4/2014 (ዋልታ) ዜጎች በዲጂታል መታወቂያ ላይ እንዲተማመኑ የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎች እየተዘጋጁ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ረቂቅ አዋጅ ግብዓት ለማሰባሰብ የሚያስችል ምክክር መደረጉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

የዲጂታል መታወቂያ ከወንጀል ጋር የተያያዙ ስጋቶችን በመቀነስ አገራዊ ደኅንነትን ለማረጋገጥም ያስችላል ተብሏል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለሚደረግ ሽግግር  ዲጂታል መታወቂያ አንዱ አስቻይ ሁኔታ መሆኑን ተናግረዋል።

የብሔራዊ መታወቂያ ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ ዘሚካኤል ዲጂታል መታወቂያ ድግግሞሽን በማስቀረት የሃብት ብክነትን በመቀነስ በነዋሪዎች መካከል ፍትሃዊነትን ለማስፈን እንደሚረዳ ተናግረዋል።