‘ዝክረ ዓድዋ’ አገር ዐቀፍ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው

‘ዝክረ አድዋ’ አገር ዐቀፍ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው
‘ዝክረ ዓድዋ’ አገር ዐቀፍ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው

የካቲት 22/2014 (ዋልታ) 126ኛ የዓድዋ ድል በዓልን አስመልክቶ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የተዘጋጀው ‘ዝክረ አድዋ‘ አገር ዐቀፍ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው።

የምዕራባዊያን የቅኝ አገዛዝ ሥርዓት አፍሪካን በተቀራመታት ወቅት ኢትዮጵያዊያን ለቅኝ አገዛዝ አሻፈረን አሉ፡፡ ታላቅ የነፃነት ተጋድሎንም ፈፅመው ወራሪውን ጦር ከኢትዮጵያ ምድር አባረሩ፤ ይህም አዲስ ታሪክ በዓለም መዝገብ እንዲፃፍ ማድረጉ ተገልጿል።
ይህ ድል በመላው አፍሪካ መቀንቀን በመጀመሩ የተቀሩት የአፍሪካ አገራት የቅኝ አገዛዝ ሥርዓትን ተዋግተው እንዲያሸንፉ ምክንያት መሆኑም ይጠቀሳል።
ይህ ትውልድ የተረከባትን ሀገር ጠብቆ በማቆየት የድል ባለታሪኮችን መዘከር ይገባዋልም ተብሏል፡፡
ዓድዋ ላይ የተለኮሰው የድል ችቦ ተቀጣጥሎ ለሌሎች አገራት የነፃነት ምክንያት መሆኑንም የታሪክ ምሁር ባህሩ ዘውዴ (ፕ/ር) ገልፀዋል።
የዓድዋ ድል ‘ነጭ ለመግዛት ጥቁር ለመገዛት ነው የተፈጠረው‘ የሚለው እሳቤም የተሳሳተ መሆኑን በተግባር የታየበት የታሪክ ገፅ መሆኑን ተናግረዋል።
“ለኢትዮጵያዊያን ኅብረት ለአፍሪካ የነፃነት ጮራ” በሚል በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ኢትዮጵያ በዓለም የነፃነት ታሪክ ላይ ያኖረችውን አሻራ የሚዳስስና የተከፈለውን የነፃነት ዋጋ የሚገልፅ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቧል።
በሃኒ አበበ