የሀረሪ ክልል ለሀገር መከላከያ ሰራዊት 14 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብና በአይነት ድጋፍ አደረገ

ሐምሌ 27/2013 (ዋልታ) – የህልውና ዘመቻ ላይ ላለው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሀረሪ ክልል በሀገር ሽማግሌዎችና በአባ ገዳዎች አማካኝነት ከክልሉ ነዋሪዎች በአጭር ጊዜ የተሰበሰበ 10 ሚሊዮን በብር እና አራት ሚሊዮን ብር በአይነት ነው ድጋፍ የተደረገው።
ክልሉ ከጥሬ ገንዘቡ ባለፈ በአይነት ድጋፍ ያደረገው 261 ካርቶን ቴምር፥ 36 ኩንታል ዳቦ ቆሎ፣ 768 ካርቶን ብስኩት፣100 ኩንታል በሶ፣ 110 ፍየልና፣ 36 የሀረር ሰንጋ በሬ መሆኑ ታውቋል።
በሀረሪ ክልል የተደረገው ድጋፍ የመጀመሪያው ነው የተባላ ሲሆን ከዚህ በኃላ በተከታታይ ድጋፋ እንዲሚቀጥል ተገልጿል።
የመከላከያ ሰራዊት የሀገርን አንድነትና ሉዐላዊነት ለማስከበር በሚያደርገው የህልውና ዘመቻ ሁሉም የበኩሉን ለመወጣት ከጫፍ ጫፍ እየተቀሳቀሰ መሆኑም ድጋፉ ዛሬ ለመከላከያ ሚኒስቴር ሲሰጥ ተነግሯል፡፡
(በምንይሉ ደስይበለው)