የሀረሪ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን የፊታችን ሐሙስ ያካሂዳል

መጋቢት 20/2014 (ዋልታ) የሀረሪ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባዔውን የፊታችን ሐሙስ ማካሄድ እንደሚጀምር የምክር ቤቱ ጽሕፈት አስታወቀ።

የጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጌቱ ነገዎ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት ምክር ቤቱ በሁለት ቀናት ጉባዔው በ6 አጀንዳዎች ላይ ይወያያል።

ምክር ቤቱ ከሚመክርባቸው አጀንዳዎች መካከልም በምስረታ ወቅት ያካሄደበት ቃለ ጉባዔ ቀርቦ እና ሰፊ ውይይት ከተካሄደበት በኋላ እንደሚጸድቅ ተናግረዋል።

እንዲሁም የአስፈጻሚ አካላት የስድስት ወራት አፈጻጸም፣ የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2012 እና 2013 ዓ ም የሴክተር መስሪያ ቤቶች የኦዲት ግኝት ፋይናሻል ሪፖርት በጉባዔው እንደሚቀርብ ተናግረዋል።

በተጨማሪም የምክር ቤቱ የአሰራር እና አባላት ሥነ ምግባር ደንብ የተሻሻለው አዋጅ ለምክር ቤቱ ቀርቦ እና  ውይይት ከተካሄደበት በኋላ ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አዋጅ ማሻሸያ እና የጠቅላይ አቃቢ ህግ ቢሮ ማቋቋምያ እና ተግባርና ስልጣንን የሚወስን አዋጅ ቀርቦ እና ሰፊ ውይይት ተካሂዶበት እንደሚጸድቅ ኃላፊው መናገራቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመልክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!