ጥር 25/2014 (ዋልታ) የሀረሪ ክልል መንግሥትና ሕዝብ አሸባሪው ሕወሓት በአማራ ክልል በከፈተው ጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል 7 ሚሊየን ብር የሚገመት የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉን ለደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጀማል አሕመድ ያስረከቡት የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙኽታር ሳሊህ በአሁኑ ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ለማለፍ ትብብርና መደጋገፍ ወሳኝ በመሆኑ ክልሉ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።
5 ሚሊየን ብር የገንዘብ እና 2 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነት ድጋፍ ማድረጋቸውን የተናገሩት ኃላፊው በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊው ጀማል አሕመድ የክልሉ ሕዝብና መንግሥት ላደረገው ድጋፍ ማመስገናቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።