“የሀሰት መረጃ በኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ያሳደረው ጫና እና መፍትሄው” በሚል የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

ታኅሣሥ 16/2014 (ዋልታ) “የሀሰት መረጃ በኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ያሳደረው ጫና እና መፍትሄው” በሚል መሪ ሃሳብ የምክክር መድረክ በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።

በምክክር መድረኩ የበቃ ዘመቻን ጨምሮ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ፣ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ በጦርነት ወቅት ታሪካዊ ዳሰሳ፣ የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙኃን የአፍሪካ ገጽታ እና ጫና በሚሉ ጉዳዮች ምክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በምክክር መድረኩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ኦባንግ ሚቶ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን አሚኮ ዘግቧል።