የሀገረመቆር – ቁንዲ ክፍል ሁለት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ

መጋቢት 26/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ መንግሥት በተመደበ አንድ ቢሊየን 580 ሚሊዮን 150 ብር የተገነባው የሀገረመቆር – ቁንዲ ክፍል ሁለት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሙሉ ለሙሉ ተጠናቋል፡፡
ፕሮጀክቱ የጨረቲ – ጎሮበቀቅሳ – ጎሮዳሞሌ – ሀገረመቆር – ቁንዲ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አካል ነው።
ከዚህ ቀደም ይስተዋል የነበረውን ከፍተኛ የትራንስፖርት እንግልት በማስቀረት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፋይዳው የጎላ እንደሚሆን ተነግሮለታል።
በአካባቢው የሚገኙትን ከፍተኛ የቁም እንስሳትና የእንስሳት ተዋፅዖ ምርቶችን በፍጥነት ወደ ገበያ ለማድረስ ማስቻሉን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር መረጃ አመላክቷል፡፡
በዋናነትም ጨረቲ ወረዳን ከጎሮበቀቅሳ እና ከጎሮዳሞሌ ወረዳ ጋር አሰተሳስሯል፡፡
ግንባታውን ያከናወነው ቻይና ኮሙዩኒኬሽን ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ሲሆን የማማከር እና የቁጥጥር ሥራን ስታዲያ ኢንጅነሪንግ ከጂ እና ዋይ ኢንጅነሪንግ በጥምረት ተከናውኗል።