የሀገር በቀል ኢንተርፕራይዞች ዓለም አቀፋዊ ዕድገትና መስፋፋት የሀገር ኩራትና የሀብት ምንጭ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ

ሰኔ 21/2014 (ዋልታ) የሀገር በቀል ኢንተርፕራይዞች ዓለም አቀፋዊ ዕድገትና መስፋፋት የሀገር ኩራት እና የሀብት ምንጭ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ራይድ አገልግሎቱን በጂቡቲ መጀመሩን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት “ራይድ ኢትዮጵያ አገልግሎታችሁን በአፍሪካ ቀንድ በማስፋት በጅቡቲ ሥራ በመጀመራችሁ እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል።

በመተግበሪያ አማካይኝነት አገልግሎት ሰጪና ተገልጋይን ያገኛኘ የትራንስፖርት ሥርዓት በመፍጠር ራይድ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW