የህንድ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ለመሰማራት ያላቸውን ፍላጎት ገለጹ

ግንቦት 16/2014 (ዋልታ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ እና ምክትል ኮሚሽነር ዳንኤል ተሬሳ ከህንድ የመጡ ባለሃብቶች እንዲሁም ከህንድ ኢኮኖሚና ንግድ ተቋም ተወካዮች ጋር ተወያዩ፡፡

ባለሃብቶቹ በኢትዮጵያ በማዕድን፣ በአምራች ዘርፍ፣ በግብርና ማቀነባበሪያ፣ በአይ ሲ ቲ እንዲሁም በትምህርት ዘርፎች ለመሰማራት ያቸውን ፍላጎት ገልጸዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ የኢትዮጵያ መንግሥት ኢንቨስትመንት የመሳብ ዕቅድን ማዕከል በማድረግ ግብዣ የተደረገለት ሲሆን በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት አሳይቷል ተብሏል፡፡

ባለሃብቶቹ የቡልቡላ፣ የቦሌ ለሚ እና የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን መጎብኘታቸውንም ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡