የህግ ማስከበር በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች መንግስት በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት እንደሚፈጸም ተገለጸ

መንግስት በትግራይ ክልል በማከናወን ላይ ስለሚገኘው ወንጀለኞችን አድኖ ለህግ የማቅረብና የህግ ማስከበር በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች መንግስት በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት እንደሚፈጸም ተገለጸ፡፡

መንግስት በትግራይ ክልል በማከናወን ላይ ስለሚገኘው ወንጀለኞችን አድኖ ለህግ የማቅረብ እና መልሶ ግንባታ ስራዎችን አስመልክቶ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት እና የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን  በጋራ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እንደገለጹት፣ መንግስት በትግራይ ክልል በማከናወን ላይ ስለሚገኘው ወንጀለኞችን አድኖ ለህግ የማቅረብ እና የመሰረተ ልማት መልሶ ግባታዎችን ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የተለያዩ ሚዲያ አካላትና የሰብዓዊ ድጋፍ ድርጅቶችና ኤጀንሲዎች በክልል መንቀሳቀስ አትችሉም ተብለናል የሚሉ ቅሬታዎችን እያቀረቡ እንደሚገኙ የጠቀሱት አምሳደር ሬድዋን፤ ይህም  መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት እንደሚፈጸም አብራርተዋል፡፡ የህግ ማስከበር በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ከማክበር ጎን ለጎን ለራሳቸውም ደህንነት ሲባል እንደሆነም ነው የገለጹት፡፡

ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በበኩላቸው እየተከናወነ ያለው የሰብዓዊ ድጋፍና አቅርቦት በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ቅንጅታዊ አሰራሩም የሚፈለገውን ድጋፉ በትክክክለ ለማድረስ እንዲያስችል በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ የእርዳት ድርጅቶችጋር በጥምረት እየተሰራም ነው ብለዋል፡፡

ኮሚሽንሩ የሰብዓዊ ድጋፉ የሚያደርጉ የእርዳታ ድርጅቶችም ከመንግስት ጎን በመሆን መንግስት በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት እንደሚፈጸም አስታውሰው ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ያላት ልምድ በመጠቀም በአጭር ጊዜ የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ይከናወናሉ ማለታቸውን ከኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመለከታል፡፡