የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን ለማክበር ለሚመጡ የትራንስፖርት አገልግሎት መዘጋጀቱ ተገለጸ

መስከረም 20/2015 (ዋልታ) የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን ለማክበር ለሚመጡ የበዓሉ ታዳሚዎች የትራንስፖርት አገልግሎት መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።

ነገ መስከረም 21 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለሚከበረው የ2015 የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን ህብረተሰቡ ለማክበር ከለሊቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ የአንበሳ፣ የሸገር፣ የድጋፍ ሰጪ እና የፐብሊክ ሰርቪስ አውቶብስ የትራንስፖርት አገልግሎት ከአባኪሮስ አደባባይ፣ ከአያት አደባባይ፣ ከቱሉዲምቱ አደባባይ፣ ከጎሮ አደባባይ፣ ከአዲሱ ገበያ፣ ከቁስቋም፣ ከሳንሱሲ፣ ከአየር ጤና አደባባይ እና ከጀሞ የትራንስፖርት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ቢሮው ማሳወቁን ኢብኮ ዘግቧል።