የመማር ማስተማር ስራው ቢጀመርም በርካታ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ መገኘት አልቻሉም- የትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር)

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከል የመማር ማስተማር ስራው ቢጀመርም በርካታ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ መገኘት አልቻሉም ሲል የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በጉዳዩ ዙሪያ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በበይነ መረብ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ወቅት ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ስራ ድጋሚ ብጀመርም፣ ወደ ትምህርት ገበታቸው ያልተመለሱ ተማሪዎች እንዳሉ ተነስቷል።

የትምህርት ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ አሳስበዋል።

ትምህርት ላይ የሚሰሩ አጋር አካላትና ከትምህርት ዘርፍ ውጭ ያሉ ተቋማትም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ያለውን ጥረት እንዲደግፉ ጠይቀዋል።

“ወደ ትምህርት ቤት እንመለስ” በሚል ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው የመመለስ ዘመቻም እንደሚጀመር ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።