በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከልን የጸጥታ ችግር ለመፍታት የሚያግዝ ህዝባዊ ውይይት ዛሬ በአሶሳ ከተማ ተጀምሯል።
በውይይት መድረኩ ከክልሉ የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ውይይቱ የሀገር አቀፉ የማህበረሰብ ምክክር መርሃ ግብር አንዱ አካል እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ዓላማው የመተከልን ሠላም መመለስ በሚቻልበት ዙሪያ ለመምከር መሆኑን የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የክልሉ የሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሳ ሃሚድ ተናግረዋል።
ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ ቀርቦ የመድረኩ ተሳታፊዎች ለመተከል ጸጥታ ችግር ምክንያት በሆኑና መፍትሄው ዙሪያ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።
ለሁለት ቀናት በሚቀጥለው የውይይት መድረክ ክልሉና ሠላም ሚኒስቴር በጋራ ያዘጋጁት መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡