የመከላከያ ሠራዊት እና የፖሊስ የደንብ ልብሶችን ለጥፋት ቡድኖች ሊያስተላልፉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ቁጥጥር ስር ዋሉ

ኅዳር 16/2014 (ዋልታ) በቡራዩ ከተማ የመከላከያ ሠራዊት እና የፖሊስ የደንብ ልብሶችን ለጥፋት ቡድኖች ለማስተላለፍ ሲዘጋጁ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎቹ በፈጠሩት ህቡዕ ህዋስ በኩል ከአዲስ አበባ ወደ ምዕራቡ የሀገሪቱ ክፍል ለማስተላለፍ እና ለአሸባሪው ሸኔ ለመስጠት ሲዘጋጁ እንደነበር የወረዳ 3 ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኢንስፔክተር ኦላና ብርሃኑ ሞሲሳ ገልጸዋል።

ኅብረተሰቡ አሁንም በያለበት አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ እና አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት ለፀጥታ ኃይሎች በፍጥነት እንዲያሳውቅ ኢንስፔክተር ኦላና ብርሃኑ ማሳሰባቸውን ኦቢኤንን ጠቅሶ ኢብኮ ዘግቧል።