የመከላከያ ሰራዊት አባላት የአሸባሪውን ግብዓተ መሬት ለመፈፀም ቃል እንገባለን አሉ

ጥቅምት 24 /2014 (ዋልታ) በሰሜን እዝ ባልደረቦቻችን ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ ስናስብ የአሸባሪውን ሕወሓት ግብዓተ መሬት ለመፈጸም ቃል በመግባት ነው ሲሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተናገሩ።

የሕወሓት አሸባሪ ቡድን ጥቅምት 24 ቀን 2013 ምሽት ላይ በሰሜን እዝ የአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በማድርስ የአገር ክህደት መፈፀሙ ይታወሳል።

አሸባሪው ቡድን በሰሜን እዝ የሰራዊት አባላት ላይ ጥቃት የፈፀመበትን 1ኛ ዓመት በመከላከያ ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ ታስቧል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ ከተገኙት መካከል የሰራዊት አባላት በሰሜን እዝ ባልደረቦቻችን ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ ስናስብ የአሸባሪውን ሕወሓት ግብዓተ መሬት ለመፈጸም ቃል በመግባት ነው ሲሉ ለኢዜአ ተናግረዋል።