የመከላከያ ሰራዊትን የሚቀላቀሉ ወጣቶች  ሽኝት

የመከላከያ ሰራዊትን የሚቀላቀሉ ወጣቶች

መስከረም 07/2014 (ዋልታ) የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባል የመሆን ጥሪን የተቀበሉ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምልምል የመከላከያ ሰራዊት ወጣቶች ሽኝት ተደረገላቸዉ።

ሽኝት የተደረገላቸዉ ምልምል የመከላከያ ሰራዊት አባላት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ ወጣቶች ናቸዉ ተብሏል።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አምሳል አማረ፣ ዞኑ ከአሁን በፊት ሀገርን ከወራሪ ለመከላከል በሚደረገዉ ጥረት በሁለት ዙር ምልምል የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ወደ ስልጠና ማዕከል መላኩን አስረድተዋል።

በሶስተኛዉ ዙር መርኃግብርም ሀገር ወዳድ ወጣቶች ተመዝግበዉ መስፈርቱን ያሟሉ ወደ ማሰልጠኛ ማዕከል እንደተሸኙ ኃላፊው ተናግረዋል።

ሽኝት የተደረገላቸዉ ምልምል የሰራዊት አባላት በማሰልጠኛ ማዕከልም ይሁን በግዳጅ በተሰማሩባቸዉ ቦታዎች ሙያዊ ግዴታቸዉን እንዲወጡ አቶ አምሳል መልዕክት አስተላልፈዋል።

አሚኮ እንደዘገበው ምልምል ወጣቶቹም ስልጠናቸዉን አጠናቀዉ የሀገራቸዉን ዳር ድንበር ለማስከበርና ወራሪዉን የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ ዝግጁ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡