የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ለአቅመ ደካማ ማህበረሰቦች ድጋፍ አደረገ

ሐምሌ 29/2014 (ዋልታ) የመከላከያ ዋር ኮሌጅ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ አቅመ ደካማ ማህበረሰቦች ድጋፍ አደረገ።

ኮሌጁ ድጋፋን ያደረገው በአዲስ አበባ ከተማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በወረዳ 02 ለሚገኙ 50 አቅመ ደካማ አባወራ እና እማወራዎች እዲሁም በዝቅተኛ ደመወዝ ተቋሙን ለሚያገለግሉ 170 ሲቪል ሰራተኞች ነው።

የድጋፍ አይነቱ መኮረኒ፣ ፓስታ፣ ዘይት የመሳሰሉ ምግብ ነክ እንዲሁም የተለያዩ አልባሳቶች እና ጫማዎች መሆናቸው በርክክቡ ተገልጿል።

በርክክብ ስነ ስርአቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ኮማንዳንት ብ/ጀኔራል ቡልቲ ታደሰ ድጋፍ ለሚሹ የማህበረሳባችን ክፍሎች ጊዜያዊ ችግር የሚቀርፍ ድጋፍ በማድረጋችን እጅግ ደስተኞች ነን ብለዋል።

የወረዳ 02 የህብረተሰብ ተሳትፎ እና የበጎ አድራጎት ማስተባባሪያ ፅ/ቤት ኃላፊ መኮነን ዘነበ በበኩላቸው የሀገራችን ዳር ድንበር በመጠበቅ የሰላማችን ዋስትና የሆነው መከላከያችን ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻችን ችግራቸውን የሚቀርፍ ወቅታዊ ድጋፍ በማድረጉ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል።

የተደረገው ድጋፍ ወደ ብር ሲቀየርም ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመለክታል።