የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እየመከሩ ነው

ነሐሴ 11/2014 (ዋልታ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ነሐሴ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ከአስቸኳይ ጉባኤው አጀንዳዎች ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው፡፡

በስብሰባው የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ፣ የመንግሥታት ግንኙነት፣ የዴሞክራሲያዊ አንድነትና የሕገ መንግሥት አስተምህሮ፣ የድጎማና የጋራ ገቢዎች ድልድል ጉዳይ እና የሕገ መንግሥት ትርጉምና ውሳኔ አፈጻጸም ክትትል ቋሚ ኮሚቴዎች ናቸው እየተሳተፉ የሚገኙት፡፡

ቋሚ ኮሚቴዎቹ በአጀንዳዎቹ ላይ በመምከር ለምክር ቤቱ የውሳኔ ሃሳቦችን ያቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡