የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀጠለ ውይይት

መስከረም 13/2014 (ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) ዋና አስተዳዳሪ አሺም ስታይነር ጋር በኒውዮርክ ተወያዩ፡፡

ውይይቱ በልማት፣ በሰላም ግንባታ እና በልዩ ልዩ የትብብር መስኮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄፔ ኮፎድ ጋር በኒው ዮርክ ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ በልማት ትብብር እና በሰብዓዊ አገልግሎት ዙሪያ ያተኮረ እንደነበር ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።