ሐምሌ 29/2013 (ዋልታ) – የሞሀ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር አመራር እና ሰራተኞች በቦሌ አራብሳ 1 ሺህ ችግኞችን ተከሉ።
ድርጅቱ ከመደበኛ ስራው በተጨማሪ ሰራተኞቹን በማሳተፍ ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ታውቋል።
ከሳምንት በፊት በሀዋሳ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እንደተከናወነ የገለፁት ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አ/ማ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ቢርቦ ከ150 በላይ ሰራተኞችን በማሳተፍ 1 ሺ ችግኞችን በቦሌ አራብሳ ተክለዋል።
ችግኞችን ከመትከል ባለፈ በመንከባከብ ቦታውን የመዝናኛ ፓርክ ለማድረግ እንደታሰበ ገልፀዋል።
በዚህ የክረምት መርሃግብር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አንድ ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን የክፍለ ከተማው ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ሲልአምላክ ገልፀዋል።
(በነፃነት ፀጋይ)