የሞሪታኒያ ፕሬዝዳንት አዲስ አበባ ገቡ

ጥር 27/2014 (ዋልታ) የሞሪታንያ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ኡልድ ኤል-ጋዝዋኒ በ35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ።

ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በተመሳሳይም የዓለም ዐቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ እና የዓለም ዐቀፍ የፍራንኮፎን ድርጅት ዋና ዳይሬክተሮች ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://www.facebook.com/waltainfo

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!