የሠመራ ዩኒቨርስቲ 1 ሺህ 887 ተማሪዎችን ለ12ኛ ጊዜ እያስመረቀ ነው

የሠመራ ዩኒቨርስቲ

ሰኔ 23/2013 (ዋልታ) – የሠመራ ዩኒቨርስቲ በ33 የትምህርት መስክ ያስተማራቸውን 1 ሺህ 887 ተማሪዎችን ለ12ኛ ጊዜ በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ነው።

ዩኒቨርስቲው በዘንድሮ ዓመት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለሁለተኛ ጊዜ ያስመረቀ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በ2013 ዓ.ም ከ3 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ከተማራቂዎች መካከል 55ቱ የሁለተኛ ድግሪ ምሩቃን ሲሆኑ፣ በአጠቃላይ ከሚመረቁት ውስጥ በኢንጀነሪንግ እና በማህበራዊ ሳይንስ የሚመረቁት ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ ነው የተባለው፡፡

የሠመራ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አደም ቦሪ ለተመራቂዎች ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ አንድም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሌላ በኩል የተለያዩ አለም አቀፍ ጫናዎች እየደረሰባት ባለበት በዚህ ጊዜ ወደ ስራው ዓለም መቀላቀለችሁ ሀላፍነታችሁን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል ብለዋል።

የሠመራ ዩኒቨርስቲ ተመራቂዎች በሀገሪቱ ለሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በስከነ ሁኔታ በመመልከት የመፍትሄ ሃሣብ አመንጪ እንዲሆኑም አሳስበዋል፡፡

ፕራዝዳንቱ አክለውም የሠመራ ዩኒቨርስቲ ተመራቂዎች በአፋር ክልል በነበራችሁ ቀይታ ከአፋር ህዝብ የተማራችሁትን ሀገር ወዳድነት፣ መተባበርና መደጋገፍ በሄዳችሁበት ሁሉ አንድተገብሩም ጠይቀዋል፡፡

(በመስከረም ቸርነት)