የሠራዊቱ አካላዊ፣ ሞራላዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ዝግጁነት የተሟላ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ

ግንቦት 11/2014 (ዋልታ) የሠራዊቱ አካላዊ፣ ሞራላዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ዝግጁነት የተሟላ ደረጃ ላይ መድረሱን የማዕከላዊ ዕዝ ኢንስፔክሽን ቡድን ገለጸ።

ኢንስፔክሽን ቡድኑ በዕዙ የግዳጅ ቀጣና ተዘዋውሮ የሠራዊቱ ትጥቅ፣ የአካል ብቃት፣ ሞራላዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ዝግጁነቱ የተሟላ መሆኑን አረጋግጧል።

የዕዙ ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር ኮሎኔል አብዱጀባር መሐመድ እንዳሉት ሠራዊቱ ላብ ደምን ያድናል በሚል ተቋማዊ መርሕ እየተመራ ቀን ከሌት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የተሰጡትን ዘርፈ-ብዙ ሥልጠናዎች በብቃት አጠናቆ በሁሉም መስክ ዝግጁ መሆኑ ተረጋግጧል።

የማዕከላዊ ዕዝ ሥልጠና ቡድን መሪ ተወካይ ሌተናል ኮሎኔል መላኩ አበጀ በበኩላቸው ተቋሙ ባወጣው የሥልጠና ዕቅድ በመመራት እና የጠላትን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ወታደራዊ ሥልጠና በማድረግ ጠንካራ ኃይል መገንባት ችለናል ብለዋል።

የማዕከላዊ ዕዝ ሊያጋጥመው የሚችለውን ማንኛውንም ጠላት መደምሰስ በሚያስችለው ወታደራዊ ዝግጁነት ላይ እንደሚገኝም ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW