የሩሲያ ሚሳኤል በዩክሬን ግድብ ላይ ጥቃት አደረሰ

መስከረም 5/2015 (ዋልታ) የሩሲያ ሚሳኤል በዩክሬን ግድብ ላይ ጥቃት ማድረሱ ተገለጸ፡፡

ሚሳኤሉ ዋነኛ የሚባል የውሃ ማጠራቀሚያ ግድብ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ በደቡባዊ ዩክሬን ከተማ የሚገኙ ባለስልጣናት ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ አሳስበዋል።

ጥቃቱ ክሪቭ ሪህ በተባለችው ከተማ የጎርፍ መጥለቅለቅ ያስከተለ ሲሆን ሁለት ወረዳዎችም በከፍተኛ አደጋ ላይ ናቸው ሲሉ የከተማዋ አስተዳዳሪ ኦሌክሳንደር ቪልኩል አስጠንቅቀዋል።

ባለስልጣናቱ እንደተናገሩት ግድቡን ጥሶ በሰኮንድ 100 ሜትር እየፈሰሰ ያለው ውሃ የኢንሁሌትስ ወንዝን በአደገኛ ሁኔታ እንዲጨምር አድርጎታል።

ሩሲያ በግድቡ ላይ ያደረሰችውን ጥቃት ዩክሬን በቅርቡ ለወሰደችው የመልሶ ማጥቃት የበቀል እርምጃ ነው ስትል መፈረጇን ቢቢሲ ዘግቧል።

ረቡዕ ዕለት ካራቹኒቭስኬ ግድብ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሩስያን “አሸባሪ መንግሥት” ሲሉ ጠርተውታል።

ጎርፉ ያጥለቀለቃት ክሪቪ ሪህ የተወለዱት ፕሬዝዳንቱ “ንጹሃንን የምትዋጉ ደካማዎች ናችሁ” በማለት ትናንት ምሽት ባደረጉት ንግግር ወርፈዋቸዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW