አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል የመንግስትን የሰላም ጥሪ ለተቀበሉ የቀድሞ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች ሹመት ሰጥቷል፡፡
በዚህ መሰረትም፡-
- አቶ ያደሳ ነጋሳ————-በቢሮ ሃላፊ ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ
- አቶ ኦሮሚያ ረቡማ ———– የኦሮሚያ ክልል ዓቃቤ ሕግ ምክትል ሃላፊ
- አቶ ቶሌራ ረጋሳ ————— የኦሮሚያ ክልል ጸጥታና አስተዳደር ቢሮ ምክትል ሃላፊ ሆነው መሾማቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡