የሰሜን ምስራቅ አካባቢ የኦፕቲካል ፋይበር መስመሮች ጥገና ተጠናቀቀ 

የኦፕቲካል ፋይበር መስመሮች ጥገና

መጋቢት 23/2014 (ዋልታ) በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ሕወሓት በከፈተው ጦርነት ከፍተኛ ውድመት አጋጥሞ የነበረውን የከፍተኛ ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች እና የኦፕቲካል ፋይበር ገመዶች የመጠገን ሥራ ተጠናቀቀ፡፡

ከደብረሲና – ሸዋሮቢት – ከሚሴ – ኮምቦልቻ – አቀስታ – ዓለም ከተማ ባለ132 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር፣ ከደብረ ብርሃን – ኮምቦልቻ – ሠመራ  እና ከኮምቦልቻ – አላማጣ እስከ ቆቦ ድረስ ባለ 230 ኪሎ ቮልት መስመር ላይ ጥገና ተጠናቋል፡፡

በተመሳሳይ ከደሴ – ወልዲያ ባለ 66 ኪሎ ቪልት መስመር ጥገና ተጠናቆ የወልዲያ እና አካባቢው ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡፡

በቀጣይ መስመሩ አገልግሎት እየሰጠ ችግሮች ቢገጥመው ችግሩን የሰሜን ምስራቅ ሪጅን የጥገና ቢሮ እንዲፈታው እና እንደሚከሰተው ችግር ስፋት ደግሞ እገዛ በሚያስፈልገው ቦታ ላይ ከማዕከል የሚንቀሳቀስ የቴክኒክ ድጋፍ ቡድን እገዛ እንዲያደርግ አቅጣጫ መቀመጡም ተመላክቷል፡፡

 

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!