የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን በሕወሓት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት 350 ሺሕ ዶላር መመደቡ ተገለጸ

ታኅሣሥ 4/2014 (ዋልታ) የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን በሕወሓት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችል የ350 ሺሕ የአሜሪካን ዶላር መመደቡ ተገልጿል።

ፌዴሬሽኑ በሕወሓት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት 350 ሺሕ የአሜሪካን ዶላር በመመደብ 100 ሺሕ ወዲያውኑ በማስረከብ ቀሪውን በ5 ዓመት ለመላክ መወሰኑን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።

ይህ ምሳሌያዊ በጎነት ሲታወስ ይኖራል ያሉት አምባሳደር ፍጹም ቦርዱንና ለጋሾችን አመስግነዋል።