ጥር 9/2015 (ዋልታ) የቱርክዬ የደህንነት ዋና ኃላፊ ሀካን ፊዳን የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር አብዱል ፈታ አልቡርሀን እና ምክትላቸው አህመድ ደጋሎ (ሀሚቲ) ጋር ተወያዩ፡፡
በካርቱም በተደረገው ውይይት ላይ የሱዳን የፀጥታ እና ደህንነት ኃላፊ አህመድ ኢብራሂም ሙፈደልም መታደማቸው ታውቋል፡፡
መሪዎቹ የፀጥታ እና ደህንነት መረጃዎችን በሚለዋወጡበት ሂደት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ መመያየታቸው የሱዳን ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡
ቱርክዬ በሱዳን የወታደራዊ አስተዳደር ሥርዓት ወደ ሲቪል አስተዳደር እንዲሸጋገር የበኩላቸውን ጥረት እያደረጉ ካሉ ሀገራት መካከል አንዷ ነች፡፡