የሲዳማ ክልል ምስረታ1ኛ ዓመት በዓል ሊከበር ነው


ሰኔ 24/2013 (ዋልታ) – የሲዳማ ክልል መዲና በሆነችው በሐዋሳ ከተማ እሁድ ሰኔ 27/2013 ዓ.ም በክልል ደረጃ ለሚከበረው 1ኛ ዓመት የክልሉ ምስረታ በዓል ቅድመ-ዝግጅት ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የሐዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በከተማው በአሉ በድምቀት እንዲከበር የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እንዲደረግ ከአመራሩ ጋር መክረዋል።
በከተማው ከሚደረጉ አበይት በዓላት ትልቁና ዋነኛው የክልሉ ምስረታ በዓል ነው ያሉት ም/ከንቲባው ይህንን ሊመጥን የሚችል ዝግጅት ሊደረግ ይገባልም ብለዋል።
በዓሉ በክልል በሁሉም አከባቢዎች የሚከበር መሆኑንን ከሐዋሳ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳይ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡