የሲዳማ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

ሚያዝያ 26/2014 (ዋልታ) የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡
የክልሉ ምክር ቤት አባላት ላለፉት ሁለት ቀናት ስልጠና ላይ ከቆየ በኋላ ነው ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ የጀመረው።
የክልሉ መንግሥት የአስፈፃሚ አካላት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ለምክር ቤቱ ቀርቦ ውይይት ማድረግ፣ የክልሉ ተጨማሪ በጀት ማፅደቅና የተለያዩ ሹመቶች ለምክር ቤቱ ማቅረብ በዕለቱ ለጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎች እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!