የሲዳማ ክልል በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች 20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

የካቲት 11/2014 (ዋልታ) የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሶማሌ ክልል በተከሰተ ድርቅ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና ልዑካቸው ድጋፉን ለሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ አስረክበዋል።

የሶማሌ ክልል ባለው የመልክዓ ምድር አቀማመጥ እና የመልማት አቅም ለቀጣይ የኢትዮጵያ ብልፅግና ዋልታና መሰረት መሆን የሚችል ክልል መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገልጸዋል፡፡

አክለውም በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የደረሰውን ጉዳት ለመቀነስ መንግሥት እያደረገ ያለውን ጥረት ማድነቃቸውን ኢብኮ ዘግቧል።