የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን እየተከበረ ነው

ሚያዝያ 14/2014 (ዋልታ) የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን በተለያዩ መንፈሳዊ ሥርዓቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡
በልደታ ማርያም ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን የዕምነቱ ተከታዮች የስቅለት በዓልን በሥርዓተ ስግደትና በጸሎት ሥነ ሥርዓት እያከበሩ ነው የሚገኙት፡፡
በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጅን ለማዳን ሲል የተቀበላቸውን መከራዎች ለማስታወስ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በሌላው ዓለም በሚገኙ የክርስቲያን ማኅበረሰብ ዘንድም እየተከበረ ይገኛል፡፡
በሳሙዔል ሓጎስ