የስቅለት በዓል በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከበረ

የስቅለት በዓል

ሚያዝያ 25/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከብሮ ዋለ።

በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በተከናወነው ሥነ ስርዓት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናትና ምዕመናን በተገኙበት በጸሎትና በስግደት ተከብሯል።

በትናንትናው እለት የጸሎተ ሐሙስ “ሕፅበተ እግር” ሥነ ስርዓት በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ መከበሩ ይታወቃል።

የፊታችን እሁድ ደግሞ የፋሲካ በዓል በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል።