የስቅለት በዓል ዛሬ በተለያዩ የዓለም ሀገራት ተከብሮ ዋለ

የስቅለት በዓል

ሚያዝያ 14/2014 (ዋልታ) የእየሱስ ክርስቶስ ስቅለት የሚታሰብበት የስቅለት በዓል ዛሬ በተለያዩ የአለም ሀገራት ተከብሯል፡፡

በዓሉ በተለይም በሺሕዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች በተገኙበት በግብፅ ኮፕቲክ ቸርች ክርስቶስ መስቀል ተሸክሞ በመጓዝ ስቃይና መከራ እንደተቀበለ በሚታመንበት መንገድ በማሰብ በፀሎት ታስቦ ውሏል፡፡

በግብፅ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኦርቶዶክስ አምነት ተከታዮች ከእየሱስ ስቅለት በፊት የነበሩትን ክስተቶች በማሰብ “ታላቅ አርብ” በመባል የሚታወቀውን የስቅለት በዓል አክብረዋል፡፡

በተመሳሳይ በዓሉ በግሪክ የተከበረ ሲሆን መልካም አርብ የእየሱስን መሰቀል ክብር በሚያሳይ የመልኩ ተከብሯል፡፡

ይህ በዓል የእየሱስ ክርስቶስ ስቅለት እና በምድረ በዳ ያደረገውን ጉዞ እንዲሁም ዳግም ወደ ኢየሩሳሌም የገባበትን በመዘከር ነው የተከበረው፡፡

በዓሉ በቡልጋሪያም በርካታ ክርስቲያኖች በልዩ አገልግሎት ተገኝተው በመጸለይ ያከበሩ ሲሆን በሀገሪቱ አብዛኞቹ የመንግሥት እና የንግድ ድርጅቶች ተዘግተዋል፡፡

በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ታስቦ የሚውለው የስቅለት በዓል ባሳለፍነው ሳምንት በተለያዩ ዓለም ሀገራት ተከብሮ እንደዋለም ይታወሳል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW