የሶማሊ ክልል የፀጥታ ኮሚቴ 4 ውሳኔዎችን አሳለፈ

ጥቅምት 22/2014 (ዋልታ) የሶማሊ ክልል የፀጥታ ኮሚቴ በሳምንታዊ ስብሰባው 4 ውሳኔዎችን አሳለፈ።
ስብሰባውን የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ መሀመድ የመሩ ሲሆን የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የፀጥታ አካላት በተገኙበት በወቅታዊ አገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ መረጃ ይጠቁማል።
በውይይቱ መጨረሻም ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮችን ትኩረት መስጠት፣ የክልሉን ውስጣዊ ሰላምና ፀጥታ ማጠናከር፣ ከጎረቤት አገራት ጋር ያለውን ድንበር በንቃት መጠበቅና ሽብርተኛ ቡድኖች ወደ ክልሉ እንዳይገቡ መከላከል እንዲሁም የብሔር ግጭቶችን ለማስነሳት የሚያሴሩ አካላትን በንቃት መከታተል የሚሉ ውሳኔዎች ተላልፈዋል።